የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግን የተቀላቀለው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በመጪው እሁድ ግንቦት 18, 2016 ዓ.ም ከአርባምንጭ ከነማ ጋር የፍፃሜ ጨዋታውን የሚያከናውን ይሆናል።
ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ለፍፃሜው ጨዋታ ይረዳው ዘንድ ጎፍ በሚገኘው የክለቡ ሜዳ ጠንካራ ልምምድ እየሰራ ይገኛል።
በከፍተኛ ሊጉ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የምድብ ሀን በበላይነት ሲያጠናቅቅ አርባምንጭ ከነማ ምድብ ለን በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል።
እሁድ 8 ሰዓት በአበበ ቢቄላ ስታዲየም ጨዋታው የሚከናወን ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራሮች እና ሰራተኞች በስታዲየም ተገኝታችሁ ክለባችሁን እንድታበረታቱ ጥሪ እናስተላልፋለን።