ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ዛሬም ድል ቀንቶታል

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ዛሬም ድል ቀንቶታል

በ18ኛው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማን ሶስት ለባዶ በማሸነፍ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሙሉ በሙሉ የጨዋታ የበላይነት በወሰደበት በዚህ ጨዋታ የማሸነፊያ  ጎሎችን የአጥቂ መስመር ተጨዋቾቹ መሳይ ሰለሞን፣ አቤል ሀብታሙ እና ልዑልሰገድ አስፋው በ8ኛው፣ በ37ኛው እና በ92ኛው ደቂቃ አስቆጥርዋል።

የኢትዮ-ኤሌክትሪክ የግራ መስመር ተመላላሽ ተጫዋች ያሬድ የማነ የጨዋታው ኮከብ በመሆን ተመርጧል።

የዛሬውን ድል ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ42 ነጥብ እና በ21 ንፁህ ጎል የከፍተኛ ሊጉን በመምራት ላይ ሲሆን አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በ29 ነጥብ ይከተላል።

ወደነበረበት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ለመመለስ በጥሩ ግስጋሴ ላይ የሚገኘው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በመጪው  ሚያዝያ 01 ቀን 2016 ዓ.ም ከንብ ክለብ ጋር 19ኛ የሊግ ጨዋታውን የሚያከናውን ይሆናል።

“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top