በሐዋሳ ስቴዲየም በተከናወነ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ወልድያ ከተማን ሶስት ለሁለት በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
ሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ ብርቱ ፉክክር ባሳዩበት በዚህ ጨዋታ የኢትዮ-ኤሌክትሪክን የማሸነፊያ ሁለት ጎሎች መሳይ ሰለሞን አንድ ጎል ደግሞ አቤል ሀብታሙ አስቆጥረዋል።
በጨዋታው ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረው መሳይ ሰለሞን የጨዋታው ኮከብ በመሆን የማሊያ ሽልማት ተበርክቶለታል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ39 ነጥብ ሊጉን ሲመራ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ኦሮሚያ ፖሊስ ክለብ በ11 ነጥብ ልዩነት ይከተላል።
18ኛው ሳምንት የከፍተኛ ሊግ መርሐግብር በመጪው ማክሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ጋር ይጫወታል።