
በጋና አክራ በተካሄደው የመላው አፍሪካ አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።
በውድድሩ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ካገኘቻቸው 18 ሜዳሊያዎች መካከል የኢትዮ ኤሌክትሪክ አትሌቶች አምስት ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አስገኝተዋል።
በሻምፒዮናው ከተሳተፉት አስራ አራት የኢትዮ-ኤሌክትሪክ አትሌቶች መካከል ሶስቱ ወርቅ ሲያገኙ ሁለቱ የብር ሜዳሊያ አግኝተዋል።
ሀጎስ ገ/ህይወት በ5 ሺህ ሜትር፣ ሳሙኤል ፍሬው በ3 ሺህ መሠናክል እንዲሁም ሂሩት መሸሻ በአንድ ሺህ 500 ሜትር ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ ያስገኙ የኢትዮ – ኤሌክትሪክ አትሌቶች ናቸው።
በተጨማሪም ብርቱካን ሞላ በሴቶች 5 ሺህ ሜትር እንዲሁም ገመቹ ዲዳ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር የብር ሜዳሊያ ለሀገራቸው አስገኝተዋል።
በዚህ አህጉራዊ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ሰባት ወርቅ፣ ሰባት ብር እና አራት ነሐስ በድምሩ አስራ ስምንት ሜዳሊያ በመሠብሰብ ናይጄሪያን ተከትላ ከአፍሪካ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።
“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



