ኢትዮ – ኤሌክትሪክ በሊጉ የመጀመሪያውን ድል አስመዘገበ

ኢትዮ – ኤሌክትሪክ በሊጉ የመጀመሪያውን ድል አስመዘገበ

በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው 4ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ባህር ዳር ከተማን 1 ለባዶ በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ኢትዮ – ኤሌክትሪክ በ16ኛው ደቂቃ ላይ አቤል ሀብታሙ ባስቆጠራት ጎል የመጀመሪያውን አጋማሽ መምራት ችሏል፡፡

ለማሸነፍ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ባህርዳር ከተማ ቢሆንም ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ያገኘውን ዕድል ወደግብ በመቀየር 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል፡፡

ኢትዮ – ኤሌክትሪክ በውድድር ዘመኑ 4 ጨዋታዎችን አድርጎ በሁለቱ አቻ ሲወጣ፣ በአንዱ ተሸንፎ የዛሬውን ጨዋታ አሸንፏል፡፡

ሁለቱ ክለቦች ከዚህ በፊት በተገናኙባቸው ሁለት ጨዋታዎች ባህርዳር ከተማ ማሸነፉ አይዘነጋም፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top