ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በሊጉ ነጥብ ተጋርቷል

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በሊጉ ነጥብ ተጋርቷል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ትናንት በተከናወነው ጨዋታ የምድቡ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪነቱን ማጠናከር የሚችልበትን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

ከሃላባ ከተማ ጋር በሐዋሳ የተጫወተው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለምንም ጎል ባዶ ለባዶ ተለያይቷል፡፡

በጋለ የጨዋታ ስሜት በጀመረው በዚህ ጨዋታ ሀላባ ከተማ በመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች የጨዋታ ብልጫ መውሰድ የቻለ ሲሆን ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በበኩሉ መሪነቱን ለማጠናከር በመልሶ ማጥቃት በጥሩ ኳስ ቅብብል ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ክልል ሲገቡ ተስተውሏል።

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ44ኛው ደቂቃ በአቤል ሀብታሙ አማካኝነት አደገኛ ሙከራ ያደረገ ሲሆን ከመስመር የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ለማስቆጠር ያደረገውን ሙከራ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል።

ከዕረፍት መልስ ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሀላባን ቁጥር ማነስ በመጠቀም ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ መድረስ ቢችልም ሙሉ በሙሉ ሲከላከል የዋለውን የሀላባን ተከላካይ መስመር አልፎ ግብ ማስቆጠር አልቻለም።

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ምንም እንኳ ነጥብ ቢጥልም በ32 ነጥብ ከተከታዩ አዲስ አበባ ከተማ በስድስት ነጥብ ርቆ የከፍተኛ ሊጉን እየመራ ይገኛል፡፡

የሃላባ ተጫዋች የሆነው አብዱልከሪም ራህማቶ በአቤል ሀብታሙ ላይ በሰራው ከባድ ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል፡፡

“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top