ኢትዮ- ኤሌክትሪክ በሊጉ ነጥብ ተጋራ

ኢትዮ- ኤሌክትሪክ በሊጉ ነጥብ ተጋራ

10ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ከቤንች ማጂ ቡና ጋር ያለምንም ጎል ተለያይቷል።

በዛሬው ዕለት በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም በተካሄደው መርሐ ግብር ሁለቱም ቡድኖች ተመጣጣኝ የጨዋታ ፉክክር አሳይተዋል።

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ኳስን መስርቶ በአጭር የኳስ ቅብብል ወደ ሜዳ ቢደርስም በርካታ ያለቀላቸው ኳሶችን አምክኗል።

ቤንች ማጂ ቡና በበኩሉ ረጃጅም ኳሶች ቶሎ ቶሎ በተቃራኒው ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ግብ ክልል መድረስ የቻለ ቢሆንም ጠንካራውን የኢትዮ-ኤሌክትሪክ የተከላካይ ክፍል ግን ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

በዛሬው ጨዋታ ነጥብ ተጋርቶ የወጣው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ22 ነጥብ እና በስምንት ንፁህ ጎል ሊጉን እየመራ ይገኛል።

ኢትዮ – ኤሌክትሪክ በመጪው ረቡዕ ጥር 01 ቀን 2016 ዓ.ም ከሞጆ ከነማ ጋር በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም የሚጫወት ይሆናል።

Scroll to Top