
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሹፌር 2ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. የጽሁፍ ፈተና ተፈትናችሁ በመንገድ ትራንስፖርት በሚፈቅደው ህግ እና ደንብ መስረት 74 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጣችሁ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 37 ለተግባር ፈተና ያለፋችሁ ስለሆነ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 18 ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እንዲሁም ከተራ ቁጥር 19 እስከ 37 ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 የታደሰ መንጃ ፈቃድ በመያዝ ኮተቤ ብረታብረት ፊትለፊት በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ተሽከርካሪ ጥገና አስተዳደር ቢሮ የተግባር ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡