የፈተና ውጤት ማስታወቂያ

የፈተና ውጤት ማስታወቂያ


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሾፌር-1ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም የውጭ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት ህዳር 17 ቀን 2018 ዓ.ም የጽሁፍ ፈተና ተፈትናችሁ በአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ደንብና መመሪያ መሰረት 74 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጣችሁ ለተግባር ፈተና ያለፋችሁ ሲሆን ፤ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 16 ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች ታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ.ም እና 17 እስከ 32 ስማችሁ የተገለጸው ታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተሽከርካሪ ጥገና አስተዳደር ቢሮ የተግባር ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top