የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጀማሪ ኤሌክትሪካል መሐንዲስ እና በጀማሪ መካኒካል መሐንዲስ የስራ መደብ ለመቅጠር ነሐሴ 07 እና ነሐሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም የጽሁፍ ፈተና መስጠቱ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም በጀማሪ ኤሌክትሪካል መሐንዲስ የስራ መደብ የጽሁፍ ፈተና ተፈትናችሁ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 15 እንዲሁም በጀማሪ መካኒካል መሐንዲስ የስራ መደብ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በተሰጠው የፅሁፍ ፈተና አብላጫ ውጤት ያመጣችሁ በመሆኑ ከመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ኮተቤ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት የሰው ኃይል ቅጥርና ምደባ ቢሮ በመገኘት የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ ቀርባችሁ የቅጥር ሂደት እንድትፈጽሙ እያሳወቅን፤ ስማችሁ ያልተገለጸው አመልካቾች የማለፊያ ውጤት ያላመጣችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡