የፕሮጀክቱ ዉጤቶች
ፕሮጀክቱ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አባይ ጮመን እና ሆሮ ወረዳዎች ይገኛል። የግንባታው ዋና ዓላማ በምስራቅ ወለጋ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች፣ በሆሮ ወረዳ እና በገጠር መንደሮች አዲስ ከተገነባው ማከፋፈያ ጣቢያ በሥርጭት መስመሮች አማካይነት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ነው። ፕሮጀክቱ 30 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 230 ኪሎ ቮልት ነጠላ ሰርኪዩት የማስተላለፊያ መስመር አለው። በሻምቡ ከተማ የተገነባው ማከፋፈያ ጣቢያ ደግሞ ባለ 230/33 ኪሎ ቮልት ሲሆን 20/25 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመር አለው።