ደጀን – ደብረማርቆስ – አሸጎዳ – ሆማት – ደሴ (ደሴ) ፕሮጀክት

ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል ደጀን ከተማ እና ደብረማርቆስ ከተማ፣ በትግራይ ክልል አሸጎዳ ከተማ፣ በአማራ ክልል ደሴ ከተማ እና በኦሮሚያ ክልል ሆርማት ከተማ ላይ የሚገነባ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የዲዛይን፣ ፍብረካ፣ ፍተሻና ሙከራ እንዲሁም የኦፕሬተሮች መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች የሲቪል ስራዎችን ያካትታል፡፡

በተጨማሪም በደጀን ከተማ ባለ 230 ኪሎ ቮልት አዲስ ማከፋፈያ ጣቢያ፣ 230 ኪሎ ቮልት መስመር የቤይ ማስፋፊያ በነባሩ የደብረማርቆስ ማከፋፈያ ጣቢያ፣ 230/33 ኪሎ ቮልት ትራንስፎርመር ቤይ ማስፋፊያ በአሸጎዳ ማከፋፈያ ጣቢያ፣ ከደብረማርቆስ እስከ ደጀን 48 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ባለ ሁለት ጥምር 230 ኪሎ ቮልት ባለ 3-ፌዝ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ፣ የኦፕቲካል ፋይበር ዝርጋታ፣ ጋልቫናይዝድ የሆኑ የብረት ጥልፍልፍ ማማዎች የፍብረካ፣ ተከላ፣ ፍተሻና ሙከራ ሥራዎችን ይይዛል፡፡

Scroll to Top