ፕሮጀክቱ ለአዋሽ – ወልድያ የባቡር መስመር ኃይል ለማቅረብ ያለመ ነው። በፕሮጀክቱ በአዋሽ እና ወልድያ ከተሞች መካከል ባለው የባቡር መስመር ላይ ለሚገኙ 8 (ስምንት) ትራክሽን ጣቢያዎች ኃይል ለማቅረብ ታቅዷል። ይህንንም ለማሳካት ወደ 200 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ባለ 132 እና 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እና በመተሐራ፣ በደብረብርሃን እና በሸዋሮቢት ከተሞች የማከፋፈያ ጣቢያዎች የማስፋፊያ ሥራዎችን ያካትታል።