ፕሮጀክቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ይገኛል። በፕሮጀክቱ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች አካባቢ በሽግዳን እና ቲርጋ ከተሞች አዳዲስ የማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ፣ እንዲሁም በአርባምንጭ – I ነባር ማከፋፈያ ማስፋፊያ እና በአርባምንጭ – II አዲስ ማከፋፈያ ጣቢያ እና በወላይታ ሶዶ – II ነባር ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ሥራዎች ይሰራሉ፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የሚያልፉት የማስተላለፊያ መስመሮች የማከፋፈያ ጣቢያዎችን የእርድ በእርስ ትስስር ያሳድጋሉ። ይህ ፕሮጀክት የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች እና የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርክ በአርባምንጭ ሥራ መጀመራቸውን ተከትሎ እየጨመረ የመጣውን የክልሉን የኤሌክትሪክ አቅርቦት ፍላጎት ለማሟላት ያለመ ያስችላል።