የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሁለት ብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕላት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ግንባታው የሳይበር ሰኩሪቲ መመዘኛዎችን ያሟላ፣ ዘመናዊ ሶፍትዌሮች እና የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች የሚገጠሙለት በመሆኑ አሠራሩን አሁን ካለው የተሻለ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ የማዕከሉ የመቆጣጠሪያ ሥርዓት ከሁሉም የኃይል ማመንጫዎች እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ወደ ብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል የሚላኩ መረጃዎችን ከሳይበር ጥቃቶች የሚከላከል የደህንነት መሳሪያ ይኖረዋል። የፕሮጀክቱ ግንባታ በፈረንሳዩ ጄኔራል ኤሌክትሪክ እና በቻይና ሲኖ ኃይድሮ ኩባንያዎች በጋራ እየተካሄደ ሲሆን የማማከር ስራው የሚከናወነው ሂፋብ በተባለ የፊንላንድ ኩባንያ ነው።

Scroll to Top