የኢ.ኤ.ኃ. ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት

የኢ.ኤ.ኃ. ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ሜክሲኮ በሚገኘው የተቋሙ ይዞታ ውስጥ የሚከናወን ነው፡፡ ግንባታው በ20 ሺህ 792 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን ሲጠናቀቅ 62 ፎቆች ይኖሩታል። የግንባታው አጠቃላይ የወለል ስፋት 197 ሺህ 800 ካሬ ሜትር ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅ 327 ነጥብ 5 ሜትር ርዝመት ይኖረዋል፡፡ ለግንባታው 445 ሚሊየን ዶላር በጀት የሚያስፈልግ ሲሆን በ4 ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። የሕንፃው ዲዛይን የአሜሪካ የአረንጓዴ ህንፃ ካውንስል የኢነርጂ እና የአካባቢ ዲዛይን (LEED) ሥርዓት የወርቅ ደረጃ መስፈርቶችን ያሟላ ነው። ለህንፃው ፍጆታ የሚውሉ ከንፋስ እና ከፀሐይ ኃይል የሚያመነጩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የሚገጠሙለት ሲሆን ይህም የተቋሙን ተልዕኮ የሚያሳይ ይሆናል።

Scroll to Top