ፕሮጀክቱ 36 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የማስተላለፊያ መስመር እና በወራቤ ከተማ የሚገነባ ማከፋፈያ አለው። የኃይል ማስተላለፊያ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ለኢኮኖሚ ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ፣ የኢነርጂ ደህንነትን ለማረጋገጥ፣ በቡታጅራ እና ወራቤ ከተሞች ለሚኖሩ ነዋሪዎችና የንግድ ተቋማት የተረጋጋና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ እየተገባ ያለ ፕሮጀክት ነው። እ.ኤ.አ. በግንቦት 19 ቀን 2022 የተጀመረውን ይህን ፕሮጀክት እስከ ሰኔ 2024 ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡ ለፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ሁለት ዓመት ጊዜ ተመድቦለታል።