ኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ

የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ማመንጫ ፕሮጀክት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በዳውሮ ዞን ኮይሻ ወረዳ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ ከጊቤ ሦስት የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በ129 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ማመንጫ ፕሮጀክት 1800 ሜጋ ዋት አቅም ይኖረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በአሁኑ ጊዜ በግንባታ ሂደት ላይ ሲሆን ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሀብት ለዘላቂ እና ንፁህ የኢነርጂ ምርት ለመጠቀም ያላትን ፍላጎት፣ የኢነርጂ ደህንነትን የማስፈን እና የኢኮኖሚ ልማትን ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል። ግድቡ በሮለር ኮምፓክት ኮንክሪት ሙሌት እየተገነባ ሲሆን 201 ሜትር ከፍታ፣ 1012 ሜትር ርዝመት አለው፡፡ ፕሮጀክቱ በዓመት በአማካይ 6460 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ የማምረት አቅም ሲኖረው ግድቡ 6.8 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ይይዛል፡፡

Scroll to Top