የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ዞን የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክት

ቦሌ ለሚ፣ ቂሊንጦ፣ ኮዬ አቦ ማከፋፈያዎች እና አቃቂ – ኮዬ አቦ – ቦሌ ለሚ – ቂሊንጦ ማስተላለፊያ መስመር;

ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት ሀገራዊ የኑሮ ደረጃን ማሳደግ ዒላማው ያደረገ ሰፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሮችን በመተግበር ላይ ነች፡፡ ከእነዚህ ጥረቶች አንዱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መቋቋም ነው።

ፕሮጀክቱ እስከ 180 ሜጋ ዋት ፍላጎት ያላቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች በቦሌ ለሚ እና እስከ 348 ሜጋ ዋት ፍላጎት ያላቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች በቂሊንጦ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ፍላጎታቸውን በማሟላት ለአዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ለደቡብ አዲስ አበባ አካባቢዎች አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የኤክስፖርት ዘርፉ ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ የሚጠበቅበትን እንዲያበረክት እና ቀጣይነት እንዲኖረው፣ ሀገራዊ  የኢኮኖሚ ልማትን ለማፋጠን እና የአካባቢውን ነዋሪዎች የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እንዲሁም ገቢያቸውን ለማሳደግ ይረዳል።

Scroll to Top