የፕሮጀክት ውጤት
ፕሮጀክቱ 175 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን በ230 ኪሎ ቮልት ነጠላ ሰርኪዩት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር በአፍዴራ በተገነባው ባለ 230/33 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል የሚያስተላልፍ ነው።
የፕሮጀክቱ ሥራ መጀመር በአፋር ክልል የሚገኙ የገጠር ከተሞችን የሚያስፈልጋቸውን ኃይል በማቅረብ ተግባራዊ እየተደረገ ላለው የገጠር ኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ፕሮግራም አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
የፕሮጀክቱ መተግበር በሰመራ እና በአፍዴራ መካከል ሊከናወኑ ለታቀዱት የመስኖ ልማት ሥራዎች አስተማማኝ ኃይል በማቅረብ የክልሉ የአጭር ጊዜ የልማት ዕቅድ እንዲሳካ እገዛ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ወደፊት ለሚገነባው የኢትዮ – ጅቡቲ ሁለተኛ ሰርኪዩት ኢንተርኮኔክሽን ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡