ባህር ዳር – ወልዲያ – የኮምቦልቻ ሃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ፕሮጀክት

ባህርዳር – ወልድያ – ኮምቦልቻ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት

ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል የሚገኝ ሲሆን የማከፋፈያ ጣቢያ እና የማስተላለፊያ መስመር ግንባታ አለው፡፡ ማከፋፈያ ጣቢያዎቹ በባህር ዳር፣ ወልዲያ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን የማስተላለፊያ መስመሩ ደግሞ የተለያዩ ዞኖችን አቋርጦ እነዚህን ማከፋፈያዎች ያገናኛሉ።

ፕሮጀክቱ ሁለት ሥራዎች ያሉት ሲሆን አንደኛው የማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ፤ ሁለተኛው ደግሞ የማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ የማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ  የማከፋፈያ ጣቢያ ዲዛይን፣ ፍብረካ፣ ማጓጓዝ፣ የተከላ፣ ፍተሻና ሙከራ የሚይዝ ሲሆን  በባህርዳር II የ400 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ሥራ፤ በወልዲያ III ባለ 400/230/33/15 ኪሎ ቮልት አዲስ ማከፋፈያ ጣቢያ በኮምቦልቻ III ባለ 400/230/33 ኪሎ ቮልት አዲስ ማከፋፈያ ጣቢያ እና በነባሩ ኮምቦልቻ II ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ሥራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

የማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታው ከባህር ዳር II – ወልድያ – ኮምቦልቻ ባለ ኪሎ ቮልት ጥምር ሰርኪዩት የማስተላለፊያ መስመር እና ከኮምቦልቻ II – ኮምቦልቻ III 230 ኪሎ ቮልት ጥምር ሰርኪዩት እንዲሁም ወልድያ ማከፋፈያ ጣቢያ በ230 ኪሎ ቮልት በሚገባ መስመር ሊወጣ የሚችል ( LILO) ባለ 230 የማስተላለፊያ መስመር ይኖረዋል።

Scroll to Top