ፕሮጀክቱ 150 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር፣ ሶስት (3) አዳዲስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ፣ ሶስት (3) ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የማስፋፊያ ሥራ እንዲሁም ሶስት (3) ነባር ማከፋፈያ ጣቢያዎችን አቅም የማሳደግ ሥራ ይይዛል፡፡
በፕሮጀክቱ የሚከናወኑት ሥራዎች በሀገሪቱ በሦስት አካባቢዎች የሚገኙ ሲሆን መቱ – ማሻ (ኦሮሚያ እና ደቡብ ምዕራብ ክልል)፣ ፊንጫ II – ሻምቡ (ኦሮሚያክልል)፣ አዘዞ – ጭልጋ (አይከል) (አማራ ክልል) ያሉ ሉትን ከተሞች ያካትታሉ፡ ።
ፕሮጀክቱ በሎት I ሶስት አዳዲስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ በጭልጋ፣ በሻምቡና በመቱ ከተሞች እንዲሁም የቤይ ማስፋፊያ ሥራ በአዘዞ፣ ፊንጫ እና መቱ ከተሞች ላይ የሚሰራ ይሆናል፡፡ በሎት II ደግሞ በሶስት አካባቢዎች ባለ 230 ኪሎ ቮልት ነጠላ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ዝርጋታ የሚከናወን ሲሆን 40 ነጥብ6 ኪሎ ሜትር በአዘዞ – ጭልጋ፣ 30 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊንጫ II – ሻምቡ እና 71 ኪሎ ሜትር በመቱ – ማሻ መስመር ላይ ይዘረጋል፡፡