የደሴ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክትን በጥቂት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ ነው።

የደሴ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክትን በጥቂት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ ነው።

በፕሮጀክቱ እስከ አሁን 126 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያላቸው ሁለት ትራንስፎርመሮችን የመትከል፣ የሲዊችያርድ የኤሌክትሮ ሜካኒካል የብረት መዋቅሮችን የማቆም እንዲሁም የመቆጣጠሪያ ክፍልና የሠራተኞች መኖሪያ ቤቶች የግንባታ ሥራዎች ተጠናቀዋል።

በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎችን የሚያገናኙ የመሬት ውስጥ ገመዶችን የመዘርጋት፣ የቤቶችን ማጠናቀቂያ እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የመገንባት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ተቋሙ የጣቢያውን ቀሪ የግንባታ፣ የፍተሻና የሙከራ ሥራዎች እስከ መጋቢት 2019 ዓ.ም. ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።

በተጨማሪም ለማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል የሚያቀርበው  የ5 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የማስተላለፊያ መስመር የሚዘረጋበት የካሳ ግምት ሥራ እየተከናወነ ሲሆን የወሰን ማስከበሩ እንደተጠናቀቀ የግንባታ ሥራው ይጀመራልም ተብሏል።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በደሴ ከተማና በዙሪያው ለሚገኙ ወረዳዎች አስተማማኝ ኃይል ከማቅረብ  በተጨማሪ በኮምቦልቻ ከተማ በሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ያለውን የኃይል ጭነት ለማቃለል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል።

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል

Scroll to Top