የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሁናዊ ተቋማዊ ቁመና እና ግዙፍ አቅም! ⚡️ልዕልና

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሁናዊ ተቋማዊ ቁመና እና ግዙፍ አቅም! ⚡️ልዕልና

የሀገራችንን የኢኮኖሚ እመርታና የቀጣናውን የኃይል ትስስር በግንባር ቀደምትነት እየመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኦፕሬሽን፣ በፋይናንስና በመሰረተ ልማት አቅሙ ታሪካዊ ደረጃ ላይ ደርሷል!

📊 የተቋሙ አሁናዊ ገጽታ በጥቂቱ፦

የማመንጨት አቅም
ሀገራዊ የማመንጨት አቅማችን በ2017 በጀት ዓመት መጨረሻ ከነበረበት 7,919 ሜጋ ዋት በ2018 በጀት ዓመት ወደ 9,730 ሜጋ ዋት ከፍ ብሏል ፡፡ 15 የውሃ፣ 5 የንፋስ እና 1 የደረቅ ቆሻሻ በድምሩ በ21 ጣቢያዎች በማስተዳደር ላይ ይገኛል።

የኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ
ከ132 እስከ 500 ኪሎ ቮልት አቅም ያላቸው 170 የማከፋፈያ ጣቢያዎች (363 ትራንስፎርመሮች) እና 20,590.63 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ 309 ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በኦፕሬሽን ላይ ይገኛሉ።

የፋይናንስና የሀብት ግዝፈት
አጠቃላይ ተቋማዊ ሀብታችን 900.54 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን የተከፈለ ካፒታሉ 585 ቢሊዮን ብር እና የተፈቀደ ካፒታሉ 1.3 ትሪሊዮን ብር በማድረስ በሀገሪቱ ቀዳሚ የመንግሥት የልማት ድርጅት ያደርገዋል።

ታሪካዊ ትርፋማነት
ተቋማችን በ2018 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ 39.5 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ በማስመዝገብ ለዓመታት ከተዘፈቀበት ኪሳራ ሙሉ በሙሉ ወጥቷል።

የኃይል ስርጭት
በ2018 ከተመረተው ኃይል 93.5% ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ሲውል 6.5% ደግሞ ለጎረቤት ሀገራት ኤክስፖርት ተደርጓል።

ተቋማችን በ7,726 የቴክኒክና የአስተዳደር ሰራተኞቹ ትጋት ሀገራችንን በታዳሽ ኃይል የማበራት ተልዕኮውን በላቀ ብቃት እያወጣ ይገኛል!

Scroll to Top