የኤሌክትሪክ ኃይል ብክነትን መቀነስ የሀገርን ኢኮኖሚ መገንባት ነው!
የኤሌክትሪክ ኃይል ብክነት (Power Loss) ከኢኮኖሚ ጥቅሙ ባለፈ የተቋሙን የፋይናንስ አቅምና የኃይል አቅርቦት አስተማማኝነት የሚፈትን ትልቅ ጉዳይ ነው። ይህ ብክነት በሁለት ዋና ዋና መንገዶች ይከሰታል፡፡
ቴክኒካዊብክነት(Technical Loss)፦ይህ ብክነት የሚከሰተው ኤሌክትሪክ ከማመንጫ ጣቢያው ተነስቶ ለተጠቃሚዎች በሚደርስበት ረጅም መንገድ ላይ በተለያዩ ምክንያቶች የሚባክን ኃይል ሲሆን በኢንጂነሪንግ ሥራዎች የሚፈታ ነው።
- ምንጮቹ፦ በዋናነት ያረጁ የማስተላለፊያ እና የሥርጭት መስመሮች እና የትራንስፎርመሮች መጨናነቅ ናቸው።
- መፍትሔው፦ መሠረተ-ልማትን ማዘመን! ስማርት ግሪድ (Smart Grid) በመጠቀም ብክነት ያለበትን መስመር ለይቶ ማወቅና ኃይልን በከፍተኛ ቮልቴጅ በማስተላለፍ በመንገድ ላይ የሚጠፋውን ኃይል መቀነስ ይቻላል።
️⃣ የንግድ ብክነት (Commercial Loss)፦ ይህኛው ብክነት ደግሞ በገንዘብ መልክ የማይሰበሰብ ኃይል ሲሆን ከቴክኒካዊ ችግር ይልቅ ከአሠራርና ከሰዎች ንክኪ ጋር የተያያዘ ነው።
- ምንጮቹ፦ የኃይል ስርቆት (ያልተፈቀደ እና ህገ-ወጥ የኃይል አጠቃቀም)፣ የንባብና የክፍያ ስህተቶች እንዲሁም ያረጁ ቆጣሪዎች ናቸው።
- መፍትሔው፦ ስማርት ቴክኖሎጂና ሕግ ማስከበር! ስማርት ሜትሮችን (Smart Meters) እና የቅድመ-ክፍያ (Pre-paid) ሥርዓትን በመዘርጋት ስርቆትንና የገቢ ፍሰት መስተጓጎልን በአስተማማኝ ሁኔታ መግታት ይቻላል።
በአጠቃላይ የቴክኒክ ብክነትን ለመቀነስ “የኢንጂነሪንግ መፍትሔ” ሲያስፈልግ የንግድ ብክነትን ለመቆጣጠር ደግሞ “ዲጂታይዜሽንና ጥብቅ አሠራር” ወሳኝ ናቸው። ሁለቱን መቆጣጠር ከተቻለ የኃይል አቅራቢ ተቋማት የፋይናንስ አቅም ይጠነክራል፤ ለሀገር ዕድገትም ተጨማሪ ኃይል ይተርፋል! 💡
