የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ባሉበት በ25 ሜትር ራዲየስ ውስጥ ቁፋሮ ማካሄድ የሚከለክል መመሪያ ፀደቀ

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ባሉበት በ25 ሜትር ራዲየስ ውስጥ ቁፋሮ ማካሄድ የሚከለክል መመሪያ ፀደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በከተማዋ ክልል ውስጥ የሚካሄደውን የኮንስትራክሽን ማዕድናት ፍለጋ፣ ምርት እና ስርጭት የሚቆጣጠር አዲስ መመሪያ አውጥቷል፡፡

“የኮንስትራክሽን ማዕድን ፈቃድ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 191/2018” በሚል ተግባራዊ እንዲሆን የፀደቀው መመሪያው ከማዕድን ቁፋሮ ጋር በተያያዘ ይታዩ የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በመድፈን ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል።

በመመሪያው መሰረት ከከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በ25 ሜትር ራዲየስ ውስጥ ማንኛውንም ቁፋሮ ማካሄድ የተከለከለ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከመኖሪያ መንደሮችና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች በ500 ሜትር ራዲየስ ውስጥ እንዲሁም ከወንዝ ዳርቻዎች በ30 ሜትር ራዲየስ ውስጥ ቁፋሮ ማከናወን ተከልክሏል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top