የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የወራቤ ማከፋፈያ ጣቢያን ጎበኙ

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የወራቤ ማከፋፈያ ጣቢያን ጎበኙ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የተመራ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን የወራቤ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን ጎብኝቷል።

በ15 ወራት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ማከፋፈያ ጣቢያው በነገው ዕለት በይፋ ይመረቃል።

በጉብኝቱ ወቅት ዋና ሥራ አስፈፃሚው እንደገለፁት የጣቢያው ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የስልጢ ዞንና የወራቤ ከተማ አስተዳደር ያደረጉት ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚደነቅ ነው።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው በጣቢያው ከኦፕሬሽን ሠራተኞች መኖሪያ ቤት፣ ከውሃና ከተሽከርካሪ አቅርቦት እንዲሁም ከኦፕሬሽን ሥራዎች አንፃር ያለውን እንቅስቃሴ ገምግመዋል።

በማከፋፈያ ጣቢያው ዙሪያ ለሚገኙ  የአካባቢው ማህበረሰቦች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት  ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችም ተቋሙ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ በማድረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top