📌 ሀገራዊ የኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት ደርሷል። ይህም በ2017 ከነበረበት በ1 ሺህ 811 ሜጋ ዋት ወይም በ23 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።
📌 በበጀት ዓመቱ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ የአይሻ ሁለት እና የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ወደ ኦፕሬሽን ማስገባት ተችሏል።
📌 በ2018 በጀት ዓመት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ከቀረበ የኃይል ሽያጭ እንዲሁም ከተለያዩ የገቢ ምንጮች 124 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል። ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ57 ነጥብ 8 በመቶ ብልጫ አለው።
📌 ከዚህ ውስጥ 475 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ዶላር ገቢ ሲሆን ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ27 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።
📌 ተቋሙ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዕዳ ወጥቶ 39 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘት ችሏል።
📌በበጀት ዓመቱ 38 ሺህ 124 ነጥብ 78 ጌጋ ዋት ሰዓት ለማመንጨት አቅዶ 35 ሺህ 670 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል አመንጭቷል።
📌 ከዚህ ውስጥ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ51 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻ አለው።
📌 ከመነጨው ኃይል ውስጥ 33 ሺህ 24 ነጥብ 59 ጊጋ ዋት ሰዓት የኃይል ሽያጭ ተከናውኗል።
📌ከዚህ ውስጥ 93 ነጥብ 5 በመቶ ለሀገር ውስጥ እንዲሁም 6 ነጥብ 5 በመቶ ለውጭ ሀገራት የቀረበ ነው። ይህም ተቋሙ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ቅድሚያ እየተሰጠ ለመሆኑ ማሳያ ነው።
📌ከሽያጭ ከቀረበው ኃይል ውስጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 56 ነጥብ 41 በመቶ፣ የዳታ ማይኒንግ 32 ነጥብ 51 በመቶ፣) ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች 4 ነጥብ 24 በመቶ ፣ ለኬኒያ የ4 ነጥብ 8 በመቶ እንዲሁም ለጅቡቲ 1 ነጥብ 65 በመቶ የቀረበ ነው።
📌 18 የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን በተለያዬ የግንባታ ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ።
📌 ከፕሮጀክት አስተዳደር፣ ከካሳ ክፍያ፣ ከሎጂስቲክስና ከፀጥታና ስርቆት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በበጀት ዓመቱ ለተቋሙ ተግዳሮቶች እንደነበሩ አንስተዋል።







