የአዳማ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለሙያዎች ባለፉት 9 ወራት በራስ አቅም ባከናወኗቸው የጥገና ሥራዎች በከ7.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪን አድነዋል!
የአዳማ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ አይናለም ወ/ሚካኤል አእንዳስታወቁት ይህ ስኬት የተመዘገበው ጣቢያው የቴክኖሎጂ ሽግግርንና የባለሙያዎችን ክህሎት መሠረት በማድረግ በወሰደው እርምጃ ነው።
የተመዘገቡት ዋና ዋና ስኬቶች፦
✅ ራስን መቻል፦ የስዊችጊር፣ የስዊችያርድ፣ የኮሙዩኒኬሽን መቆጣጠሪያዎች እና የስርጭት መስመሮችን በራስ ባለሙያዎች በመጠገን ከፍተኛ ወጪ ተቆጥቧል።
✅ የቴክኖሎጂ ሽግግር፦ በካርዶች፣ በስሊፕሪንግ እና በአይ.ጂ.ቢ.ቲ (IGBT) የጥገና ሥራዎች ወቅት የክህሎት ሽግግር በማድረግ አዳዲስ ባለሙያዎችን ማፍራት ተችሏል።
✅ ከፍተኛ ዝግጁነት፦ ከጣቢያው 34 ተርባይኖች ውስጥ 33ቱ (96%) በአሁኑ ወቅት ኃይል ለማመንጨት ሙሉ ዝግጁነት ላይ ይገኛሉ።
✅ የዕቅድ አፈጻጸም፦ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 105.37 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ማመንጨት የተቻለ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1.5 በመቶ ብልጫ አለው።
✅ ዘመናዊ አደረጃጀት፦ የካይዘን (Kaizen) ፍልስፍናን በመከተል የዕቃ ግምጃ ቤት፣ የወርክሾፕ እና የሙያ ደህንነት ሥራዎች ተከናውነዋል።
ባለሙያዎቻችን መደበኛ የጥገና ሥራዎችን (452 የመከላከያ ጥገናዎች) በወቅቱ በማከናወናቸው፣ ተርባይኖቹ የታቀደላቸውን ንጹህ ኃይል እንዲያመርቱ እያደረጉ ይገኛሉ። የሀገር ሀብትን በመቆጠብ ለቀጣይ ትውልድ አስተማማኝ ኃይል እያቀረብን ነው!