የሀገርን ማዕዘናት በንጹህ ኃይል የማብራት ጉዞ

የሀገርን ማዕዘናት በንጹህ ኃይል የማብራት ጉዞ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን በጥቅም ላይ በማዋል የምስራቅ አፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል ለመሆን አበክራ እየሰራች ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለፁት “የታዳሽ ኃይል አማራጮቻችንን በስፋት በማሳደግ፣ የሀገራችንን እያንዳንዱን ማዕዘን እያበራን እንገኛለን” የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኤኮኖሚና በኃይል ዘርፍ የያዘችውን ሀገራዊ ራዕይና በተግባር ያሳካቻቸውን ስኬቶች ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።

ሀገርን በታዳሽ ኃይል ለማብራት ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል፡-

1. የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ

  • የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ5,150 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ግዙፍ የውሃ ኃይል ማመንጫ ሲሆን የሀገሪቱን ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ከእጥፍ በላይ አሳድጓል። ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች፣ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ለዜጎች አስተማማኝ ኃይል ከማቅረቡ ባሻገር ለጎረቤት ሀገራት ኃይል በመሸጥ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ ይገኛል።

2. የታዳሽ ኃይል ምንጮች አሰባጥሮ መጠቀም                

  • ኢትዮጵያ እንደሀገር ከውሃ ኃይል ማመንጫዎች በተጨማሪ እንደ አሸጎዳ፣ አዳማ 1 እና 2፣ አይሻ 2 እና አሰላ ያሉ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ሥራ መጀመር ከንፋስ የማመንጨት አቅምን 504 ሜጋ ዋት ያደረሱ ናቸው፡፡  ማሳደግ እንዲሁም የአይሻ የንፋስ ኃይል ፕሮጀክትን የመሳሰሉ አዳዲስ ግንባታዎችን በማጠናቀቅ የኃይል አማራጩን ማሰፋፋት ተችሏል። በአሉቶ ላንጋኖ እና በቱሉ ሞዬ እየተካሄዱ ያሉ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶች የወደፊት የኃይል ዋስትና ስብጥርን ከሚያረጋግጡ የታዳሽ ኃይል አማራጮች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዋናው ግሪድ ርቀው ለሚገኙ የገጠር አካባቢዎች የፀሐይ ኃይል አነስተኛ ግሪዶችን (Mini-grids) እና የቤት ውስጥ ሶላር ሲስተሞችን መስፋፋት የኃይል ተደራሽነትን lማሳደግ ተዐማሪ አቅም ፈጥሯል፡፡

3. የኃይል ተደራሽነትን ማፋጠን

  • በገጠርና ከከተሞች ራቅ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በሺዎች የሚቆጠሩ መንደሮችና አነስተኛ ከተሞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል፡፡ የመኖሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ጣቢያዎችና የግብርና ምርት ማቀናበሪያዎች ኃይል እንዲያገኙ በማድረግ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ጥራት ማሻሻል ተችሏል።

4. ቀጣናዊ የኃይል ትስስር

  • ኢትዮጵያ ከታዳሽ የኃይል ምንጮች የሚመነጭ ንፁህ ኢነርጂ ወደ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ በመላክ የኃይል ትስስር ፈጥራለች፡፡

5. የግል አልሚዎች ወደ ዘርፉ መግባት

  • ዘርፉን ለማዘመን በተከናወኑ የፖሊሲ ማሻሻያዎች የሀገር ውስጥና የውጭ የግል አልሚዎች (Private Developers) በኃይል ማመንጨት ሥራ ላይ በር የሚከፍት የፖሊሲ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል።

በአጠቃላይ የታዳሽ ኃይል አማራጮችን ማስፋፋት የዜጎችን የዕለት ተዕለት ህይወት ከማሻሻሉም በላይ ሀገራችንን ወደ ተሻለ የኢንዱስትሪ እና የኢኮኖሚ እድገት የሚያሸጋግር የታሪካዊ ጉዞ አወንታዊ ማሳያ ነው።

Scroll to Top