📌 የተቀናጀ የደህንነት አስተዳደርና ጥበቃ፦ ለከፍተኛ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች (ኃይል ማመንጫዎች፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎች፣ ማስተላለፊያ መስመሮች እና በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች) ዘላቂ፣ አስተማማኝ እና የተቀናጀ የደህንነት ሥርዓት መዘርጋት፤
📌 ወንጀል መከላከልና ሕግ ማስከበር፦ በመሰረተ ልማቶች ዙሪያ ሕግ የማስከበር ሥራዎችን በማጠናከር፣ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል እና ፈጣን ምርመራ በማድረግ ለዓቃቢ ሕግ ለክስ ሂደት ማቅረብ፤

📌 የመረጃ ልውውጥና የስጋት ግምገማ፦ የደህንነት ስጋት ግምገማዎችን በየጊዜው በማካሄድ ክፍተቶችን መለየት፣ መረጃዎችን መለዋወጥ እና በግኝቶቹ ላይ በመመስረት የጋራ ኦፕሬሽኖችን ማስተባበር፤
📌 አካላዊ የጥበቃ ሥራዎችና የመስመር ክትትል፦ የኃይል ማመንጫዎችን፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎችንና ፕሮጀክቶችን እንዲሁም የዋና እና ሪጅን መ/ቤቶችን መጠበቅ፤ በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ኮሪደሮች ላይ መደበኛ የጥበቃ ቅኝት በማድረግ የሚፈጸሙ ስርቆቶችን እና ሕገ-ወጥ ግንባታዎችን መከላከል፤
📌 የአደጋ ጊዜ ምላሽና ቀውስ አስተዳደር: ለደህንነት ክስተቶች፣ ለሽብርተኝነት ሥጋቶች እና ለተፈጥሮ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ የመስጠት ሥራዎችን ማከናወን እና
📌 የአቅም ግንባታና የማህበረሰብ ተሳትፎ፦ የጋራ ሥልጠናዎችን፣ የቀውስ አስተዳደርና የአደጋ ጊዜ ልምምዶችን (Emergency Drills) ማካሄድ እንዲሁም ከማህበረሰቡ እና ከየአካባቢው የመስተዳደር አካላት ጋር በመተባበር የመሰረተ ልማት ጥበቃ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎችን ማጠናከር ናቸው።

