በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ዘርፍ ያስገነባው የዕቃ መጋዘን ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
በዘርፉ የራስ ኃይል ግንባታ መምሪያ የሀብት አስተዳደር ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኪሮስ ነጋሽ እንዳስታወቁት በዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው የዕቃ መጋዘን የሥራ መገልገያ መሣሪያዎችን በአግባቡ ለማደራጀትና ለመጠበቅ እያገዘ ነው፡፡
አዲስ የተገነባው መጋዘን ያለ አግባብ በየቦታው ተቀምጠው የነበሩ ዕቃዎችን በአንድ ላይ በመሰብሰብ ከፀሐይ፣ ከአቧራ እና ከዝናብ ለመከላከል እንደሚያስችልም ነው የጠቀሱት፡፡
እንደ አቶ ኪሮስ ገለፃ የዕቃ ማስቀመጫ መጋዘኑ መገንባት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታዎችን ለማከናወን የሚረዱ በውጭ ምንዛሬ የተገዙ የተለያዩ መሣሪያችን ደህንነት ለማስጠበቅ፤ ምቹ የአሰራር ሥርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ ቀልጣፋና ዘመናዊ የቁጥጥርና ክትትል ሥራዎች እንዲከናወኑ ያግዛል፡፡
ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረገው የዕቃ ማስቀመጫ መጋዘን ከ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቢሆንም በተቋሙ በራሱ በመሰራቱ 920 ሺህ ብር ወጪ ብቻ እንደተደረገበትም ነው ሥራ አስኪያጁ የጠቀሱት፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ – ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም