አራተኛው የህብረት ስምምነት ድርድር ተጀመረ

አራተኛው የህብረት ስምምነት ድርድር ተጀመረ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሰረታዊ የሠራተኞች ማህበርና በተቋሙ ሥራ አመራር መካከል የህብረት ስምምነቱን ለማሻሻል ድርድር መጀመሩን የህብረት ስምምነቱ ኮሚቴ ሰብሳቢ ገለፁ፡፡

ሰብሳቢው አቶ ደረጄ አጥናፌ እንደገለፁት የተቋሙንና የሠራተኛውን ጥቅምና መብት ባስጠበቀ መልኩ ሥራዎች እንዲሰሩ እና የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ በኩል የህብረት ስምምነቱ ትልቅ ሚና ይኖረዋል፡፡

በሥራ ላይ ያለውን የህብረት ስምምነት ለማሻሻል አንቀፆችን ለመለየት ከተቋሙ ሥራ አመራር እና ከመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ተወካዮች የተውጣጣ ቡድን ድርድር መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በድርድሩ በሥራ ላይ ባለው የህብረት ስምምነት ላይ የቅሬታ እና የአለመግባባት ምንጮች ሆነው አላሰራ ያሉ ጉዳዮች ካሉ በጥንቃቄ ታይተው እንደሚስተካከሉ ጠቁመዋል፡፡

ለቀጣይ ሶስት ዓመታት እንዲያገለግል እየተዘጋጀ ባለው የህብረት ስምምነት ላይ ሀሳብ አለኝ የሚል የሥራ ክፍል በሰው ኃይል ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት በኩል ሀሳቡን ሊያቀርብ እንዲሚችልም ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር እና የህብረት ስምምነት ድርድር ኮሚቴ አባል አቶ ዳንኤል ገ/ሚካኤል በበኩላቸው የህብረት ስምምነቱ የተቋሙን እና የሠራተኛውን መብት እና ጥቅም ያስጠበቀ እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ከተቋሙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ግብዓቶችን በዘርፍ ተወካዮች እና በደብዳቤ መሰበሰቡን የገለጹት አቶ ዳንኤል በሦስተኛው ህብረት ስምምነት ያልተካቱቱ፣ በስራ ሂደትም እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮች በድርድሩ ሊታዩ ይችላሉ ብለዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top