የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የ15 እና በ 33 ኪሎ ቮልት ስዊችጊር ቅየራ በራስ አቅም በማከናወኑ ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማዳኑን በማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ የዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ትንተና ቢሮ አሰታወቀ፡፡
የቢሮው ሥራ አስኪያጅ አቶ ታገል ደገፉ እንዳስታወቁት ዘርፉ በ2016 በጀት ዓመት በ22 ማከፋፈያ ጣቢያዎች የ15 እና የ33 ኪሎ ቮልት ስዊችጊር ቅየራ በራስ አቅም አከናውኗል፡፡
በጣቢያዎቹ የስዊችጊር ቅየራ ለማከናወን 2 ሚሊዮን 463 ሺህ ዶላር ግምታዊ ሥራ ለመሥራት የታቀደ ቢሆንም በዘርፉ በራስ አቅም በ12 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር መስራት በመቻሉ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ወጪ ማዳን መቻሉን አስረድተዋል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት ከተጠናቀቁት የስዊችጊር ቅየራዎች በተጨማሪ የ11 ማከፋፈያ ጣቢያዎች የሥዊች ጊር ቅየራ ሥራ በስራ ሂደት መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡
“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”