የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች “ከምርጫ ድል ማግስት፤ ጠንካራ መንግሥት” በሚል መሪ ሀሳብ በተቋማዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በዋና መሥሪያ ቤት ውይይት ማካሄድ ጀምረዋል።
የውይይት መድረኩን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በንግግር የከፈቱት ሲሆን በውይይቱ ላይ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና በርካታ ቁጥር ያላቸው የተቋሙ ሠራተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የውይይት መድረኩ በዋናነት በ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ቅድመ ሂደቶችና በቀጣይ በድህረ ምርጫ በሚከናወኑ ዓበይት ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
በመድረኩ ላይ “ከምርጫ ድል ማግስት፤ ጠንካራ መንግሥት” በሚል በመንግሥት የተዘጋጀው መነሻ ሰነድ በንባብ እየቀረበ ሲሆን በቀጣይም በሰነዱ ዙሪያ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”