የገፈርሳ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በአካባቢው ለሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች አስተማማኝ ኃይል በማቅረብ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አስታወቀ።
የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ደቻሳ እንደተናገሩት ማከፋፈያ ጣቢያው በአካባቢው ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች በተለይም ለፋብሪካው የታጠቅ ቅርንጫፍ ትልቅ አቅም ፈጥሯል።
ፋብሪካው ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የኃይል አቅርቦት አንዱ ፈተና እንደነበር ያስታወሱት ሥራ አስኪያጁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በማከፋፈያ ጣቢያው የማሻሻያ ሥራ በመስራቱና የተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ በመትከሉ የፋብሪካው የማምረት አቅም በእጥፍ ማደጉን ገልጸዋል።
ቀደም ሲል በቀን በአማካይ እስከ 5 ሺህ ቶን ሲሚንቶ ያመርት የነበረው ፋብሪካው አሁን የማምረት አቅሙ በእጥፍ አድጎ በቀን ከ10 ሺህ ቶን በላይ ሲሚንቶ ማምረት መቻሉን አስረድተዋል፡፡
ፋብሪካው ተጨማሪ ሲሚንቶ ከማምረቱ ባሻገር የማምረት አቅሙ በማደጉ ተጨማሪ የሰው ኃይል መቅጠር መጀመሩን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



