የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት ላይ ላይ ከተደቀኑት ፈተናዎች መካከል አንዱና ዋንኛው ስርቆት ነው፡፡ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ የብረት ምሰሶዎች ላይ ስርቆት የሚፈፀመውን ስርቆት መከላከል ለአንድ ተቋም የሚተው ባለመሆኑ የሁሉንም ጥረት ይፈልጋል፡፡ በዚህ በኩል መሰረተ ልማቶቹ የሚገኙባቸውና አቋርጠው የሚያልፏቸው ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል፡፡