የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጤና ቡድን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጤና ቡድን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ

በመጪው ረቡዕ ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በተቋም ደረጃ የሚከበረውን የካምፓኒ ቀን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና በማዕድን ሚኒስቴር የጤና ቡድኖች መካከል በተካሄደ የእግር ኳስ ጨዋታ ኢትዮ – ኤሌክትሪክ የጤና ቡድን 8 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ጨዋታውን በፍፁም የበላይነት ተቆጣጥሮ በተጋጣሚው ላይ የጎል ናዳ አዝንቧል።

አብዛኛውን የጨዋታ ጊዜ በተጋጣሚያቸው ሜዳ ላይ ያሳለፉት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ከዚህ በላይ ጎል ማስቆጠር የሚችሉበትን ዕድል አምክነዋል።

በጨዋታው ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ኳስን ተቆጣጥሮ በመጫወት እና ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ በመድረስ ከተጋጣሚያቸው የላቀ እንቅስቃሴ ማድረግ ችለዋል።

የአጥቂ መስመር ተጫዋቹ ፈቃዱ ቃበታ አራት እና ረዳ ወልዴ ሶስት ጎል በማስቆጠር ሀትሪክ የሰሩ ሲሆን ቀሪዋን አንድ ጎል ዋሲሁን ታደሰ ከመረብ አሳርፏል።

የማዕድን ሚኒስቴር የጤና ቡድንን ብቸኛ የማስተዛዘኛ ጎል አቤኔዘር ተስፋዬ አስቆጥሯል።

የኢትዮ – ኤሌክትሪክ የጤና ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኃይሉ ወልዴ ቡድናቸው ተጋጣሚውን በመብለጥ ድል በመቀዳጀቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በመጪው ሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ስዓት ከተሽከርካሪ ጥገና የጤና ቡድን ጋር ለዋንጫ እንደሚጫወቱ ተናግረዋል።

Scroll to Top