የውጤት ማስታወቂያ

የውጤት ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በHR Administration Officer I እና በFinance Administration Officer I የሥራ መደቦች ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ መውጣቱ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት መስፈርቱን አሟልታችሁ ለተሰጠው የጽሁፍ ፈተና ከተቀመጣችሁት ተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ያለፋችሁ አመልካቾች ዝርዝር ከዚህ በታች ተገልጿል፡-

በHR Administration Officer I የስራ መደብ ከተ.ቁ 1 እስከ 25 ያላችሁ ተወዳዳሪዎች፤
በFinance Administration Officer I የስራ መደብ ከተ.ቁ 1 እስከ 15 ያላችሁ ተወዳዳሪዎች፤

በተሰጠው የጽሁፍ ፈተና አብላጫ ውጤት ያመጣችሁ በመሆኑ፣ ከጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ተቋሙ ዋና መ/ቤት የሰው ኃይል ቅጥርና ምደባ ቢሮ በመገኘት፣ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ የቅጥር ፎርም እንድትሞሉ እናሳውቃለን፡፡

Scroll to Top