የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ደግፉ። ልገሳዎ እድገትን፣ ንጹህ ሃይልን እና እድገትን ያቀጣጥላል። እያንዳንዱ ቢት ለወደፊት ብሩህ ጊዜ ሀብቶችን ይጠብቃል። ዛሬ ተፅእኖ ለመፍጠር ይቀላቀሉን።
የኃይል ሽያጭ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከተሰጡት ተልዕኮዎች ውስጥ አንዱ የኤሌክትሪክ ኃይልን በማምረት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣132 ኪ.ቮ እና ከዚያ በላይ ኃይል ለሚጠቀሙ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች እና ለጎረቤት ሀገራት በጅምላ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ ነው፡፡
በዚህም ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትም ሆነ ለከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከጎረቤት ሀገራት መካከልም ከሱዳን ጂቡቲና ኬንያ ጋር የኃይል ትስስር በመፍጠር እና በአማካኝ ከ100 ሜጋ ዋት ያላነሰ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ በየዓመቱ በአማካይ 100 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት ላይ ነው፡፡ ወደ ኬንያም በቅርቡ የኃይል ሽያጭ ጀምሯል፡፡
የኢትዮ – ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር በዓመት እስከ አንድ መቶ ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ማስገባት አቅም ያለው ሲሆን ከኬንያ አልፎ ከታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ላሉት ሀገራት እስከ ሁለት ሺህ ሜጋ ዋት ኤሌክትክ የማስተላለፍ አቅም አለው፡፡
በተጨማሪም ሀገራችንን ከምስራቅ አፍሪካ ባሻገር የአፍሪካ የኃይል ምንጭ ማዕከል በማድረግ የክፍለ አህጉሩን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር የኃይል ትስስር በመፍጠር ትስስሩን ወደ ክፍለ አህጉራዊ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው፡፡ ለዚህም የኢትዮ – ኬንያ ባለ 500 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡
በረጅም ጊዜ ዕቅድም ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሶማሌ ላንድ፣ ታንዛኒያ እና ደቡብ ሱዳን ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ለመፍጠር የሁለትዮሽ ግንኙነት በማድረግ ላይ ትገኛለች። በዚህም በቀጣይ ለእነዚህና ለሌሎች ሀገራት ኤሌክትሪክ በማቅረብ ዘርፉን ለሀገሪቱ የውጪ ምንዛሪ ከሚያስገኙ ዘርፎች መካከል አንዱ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡
ግብረ መልስ