የተጫነው አቅም በምንጭ ተካፍሎ

ከውሃ 4820.2 MW
4820.2 MW 91%
ከንፋስ 404 MW
MWnntg 7%
ከእንፋሎት 7.3 MW
2500 KW 0.5%
ባዮማስ 25 MW
2500 KW 1%
ፈጣን አገናኞች

ሃይል ማመንጨት

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ፈጣንና ተከታታይ ዕድገት ማስመዝገብ ችላለች፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ልማት ደግሞ ለዚህ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለማቋቋም በወጣውና በተሻሻለው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 381/2008 መሠረት ተቋሙ የኃይል ማመንጫዎችን፣ የኃይል ማስተላለፊያዎችንና የኃይል ማከፋፈያዎችን የመገንባት፣ የጅምላ ሽያጭ፣ የተስማሚነት ጥናት፣ የዲዛይንና የቅየሳ ሥራ የማከናወን ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ
አዳማ ንፋስ 1
ቆቃ
ጊቤ 3

በአሁኑ ጊዜ ተቋሙ 22 የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መካከል 16 ያህሉ ከውሃ ሲሆኑ እነሱም ጊቤ 3 (1870 ሜ.ዋ)፤በለስ (460 ሜ.ዋ)፤ ግልገል ጊቤ 2 (420 ሜ.ዋ)፣ ተከዜ (300 ሜ.ዋ)፣ ግልገል ጊቤ 1 (184 ሜ.ዋ)፣ መልካ ዋከና (153 ሜ.ዋ)፣ ፊንጫ (134 ሜ.ዋ)፣ አመርቲ ነሼ (95 ሜ.ዋ)፣ ጢስ ዓባይ 2 (73 ሜ.ዋ)፣ ቆቃ (43.2 ሜ.ዋ)፣ አዋሽ 2 (32 ሜ.ዋ)፣ አዋሽ 3 (32 ሜ.ዋ)፣ ጢስ ዓባይ 1 (11.4 ሜ.ዋ) አባ ሳሙኤል (6.6 ሜ.ዋ)፤ ገናሌ ዳዋ 3 (254 ሜ.ዋ.) እና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ( ሥራ የጀመሩት ሁለት ዪኒቶች 750 ሜ.ዋ.) በድምሩ ከውሃ 4820.2 ሜጋ ዋት ያመነጫሉ፡፡

ከንፋስ ደግሞ አዳማ 2 (153 ሜ.ዋ)፣ አሸጎዳ (120 ሜ.ዋ) እና አዳማ 1 (51 ሜ.ዋ) እንዲሁም በከፊል ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ (80 ሜ.ዋ) በድምሩ 404 ሜጋ ዋት በማመንጨት ላይ ሲሆን ቀሪው ከእንፋሎትና ከዲዝል መጠባበቂያ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው ነው፡፡

የማመንጨት አቅም በሜጋ ዋት (በ2015 ዓ.ም)

ተ/ቁየኃይል ማመንጫ ጣቢያው ስምከሀይድሮከነፋስከዕንፋሎትከቆሻሻጠቅላላ የማንጨት አቅም በሜጋ ዋትየሚገኝበት ክልል
1ቆቃ43.243.2ኦሮሚያ
2ጢስ አባይ I11.411.4አማራ
3አዋሽ II3232ኦሮሚያ
4አዋሽ III3232ኦሮሚያ
5ፊንጫ134134ኦሮሚያ
6መለካ ዋከና153153ኦሮሚያ
7አሉቶ ላንጋኖ7.37.3ኦሮሚያ
8ጢስ አባይ II7373አማራ
9ግልገል ጊቤ I184184ኦሮሚያ
10ተከዜ300300ትግራይ
11ግልገል ጊቤ II420420ደቡብ ክልል
12በለስ460460አማራ
13አመርቲ ነሺ9797ኦሮሚያ
14አሸጎዳ120120ትግራይ
15አዳማ I5151ኦሮሚያ
16አዳማ II153153ኦሮሚያ
17ግልገል ጊቤ III18701870ደቡብ ክልል
18አባ ሳሙኤል6.66.6ኦሮሚያ
19ረፒ ቆሻሻ2525አዲስ አበባ
20ገናሌ ዳዋ254254ኦሮሚያ
21ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ750750ቤኒሻንጉል
22አይሻ II ንፋስ8080ሶማሊያ
ጠቅላላ4820.24047.3255256.5

ግብረ መልስ

አስተያየት
Scroll to Top