የ ስራ አመራር ቦርድ አባላት

የተከበሩ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) -( የትምህርት ዝግጅት ሦስተኛ ዲግሪ )

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በአሁኑ ወቅት የኢፌዲሪ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የመከላከያ ሚኒስትር፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አጄንሲ የሳይበር ቴክኖሎጂ ኢንጅነሪንግ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ ናቸው። በሙያቸው ኤሌክትሪካል ኢንጂነር ሲሆኑ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ መልዕክት

ኢትዮጵያውያን የአባቶቻቸውንና የእናቶቻቸውን ራዕይ፣ ህልም፣ ተስፋ፣ ምኞትና መስዋዕትነት በደማቸው፣ በወዛቸው፣ በእንባቸውና በፀሎታቸው አክብረዋል፡፡ እኛም በሁሉም ረገድ፣ በተለይም በኃይል ልማት ዘርፉ የአባቶቻችንና የእናቶቻችን እውነተኛ ልጆች መሆናችንን ደግመን ደጋግመን እናረጋግጣለን። ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኢነርጂ ዋስትናን ከማረጋገጡም በላይ በቀጣይ ከታቀዱት ፕሮጀክቶች ጋር ተዳምሮ ወደ ብልጽግናችን የምንሸጋገርበት መግቢያ በራችን ነው።

የተከበሩ አምባሳደር ግርማ ብሩ - ( የትምህርት ዝግጅት በቢዝነስ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ)

ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ (MBA)፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። ቀደም ሲል ለአምስት ዓመታት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስትር እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን አገልግለዋል። በሙያቸው ኢኮኖሚስት ሲሆኑ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

የተከበሩ አይሻ መሀመድ - ( የትምህርት ዝግጅት በቢዝነስ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ወቅት የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር፣ የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስትር እንዲሁም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ናቸው፡፡ በሙያቸው ሲቪል መሐንዲስ ሲሆኑ ለሁለት አስርት ዓመታት ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

የተከበሩ ኢዮብ ተካልኝ( ዶ/ር) - ( የትምህርት ዝግጅት ሦስተኛ ዲግሪ )

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ሚኒስትር እና የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን አገልግለዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ታዋቂ የመንግሥት፣ የግል፣ ዓለም አቀፍና አካዳሚያዊ ተቋማት ውስጥ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎችን መርተዋል።
ዶ/ር እዮብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH)፣ የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ የበርካታ ተቋማት የሥራ አመራር ቦርድ አባል ናቸው። እንዲሁም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን (ERA)፣ የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) እና የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣንን (PPA) በቦርድ ሰብሳቢነት ይመራሉ። በሙያቸውም ኢኮኖሚስት ናቸው።

የተከበሩ አቶ ፍቃዱ ድጋፌ - ( የትምህርት ዝግጅት ሁለተኛ ዲግሪ )

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ወቅት የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ እና ዋና ኢኮኖሚስት ናቸው፡፡ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ በተለያዩ የፋይናንስ ዘርፎች በማክሮ ኢኮኖሚ ላይ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ቆይተዋል፡፡ በሙያቸውም ኢኮኖሚስት ናቸው።

አቶ መላኩ አለበል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደም የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የአማራ ክልል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው አገልግለዋል፡፡ በተጨማሪም በአማራ ክልል እና በፌዴራል መንግሥት የተለያዩ የአመራር ኃላፊነቶችን ተቀብለው ሰርተዋል።

ኢ/ር አሻብር ባልቻ

ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (ኢኤኃ) ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የሥራ አመራር ቦርድ አባል ናቸው።
ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ ያገለገሉ ሲሆን የውሃ እና የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን እንዲሁም የኃይል ማስተላለፊያ መሠረተ ልማቶችን በስትራቴጂያዊ መንገድ በማልማት የኢትዮጵያን የኃይል ዘርፍ በማሳደግ ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል።
ኢንጂነር አሸብር ከመካኒካል መሐንዲስነት እስከ ዋና ሥራ አስፈፃሚነት የደረሱበት የሥራ ጉዞ በኃይል ልማት ዘርፉ ላይ ሁሉን አቀፍ ዕውቀት እንዲኖራቸው አስችሏቸዋል። ይህም ቴክኒካዊ ጥራትን ከከፍተኛ የፖሊሲ እና የግንባታ አስተዳደር ጋር በማመጣጠን ለመምራት አግዟዋቸዋል። በተጨማሪም ዘላቂ የኃይል ልማት መፍትሄዎችን በማቅረብ እና የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ዕድገት ለመደገፍ ብሔራዊ የኃይል አቅርቦት መረቦችን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ የሆነ ቁርጠኝነት አላቸው።

ወ/ሮ ማህሌት ንጉስ - ( የትምህርት ዝግጅት የመጀመሪያ ዲግሪ )

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ወቅት የማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም ባለሙያ፣ የሰኩሪቲ ሞኒተሪንግ እና ምላሽ ኤክስፐርት እንዲሁም የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ተወካይ ናቸው፡፡ በሚያቸው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ ሲሆኑ ሁለት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ተቋማቸውንና ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

አቶ ተሾመ በላይ - (የትምህርት ዝግጅት በአርት ሁለተኛ ዲግሪ)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ጊዜ የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ እና የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ተወካይ ናቸው፡፡
ቀደም ሲል የግብርና ልማት ባለሙያ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከፍተኛ ሪፖርተር ሆነው አገልግለዋል፡፡ በሙያቸው የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ ሲሆኑ በተለያየ ዘርፍ ሁለት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ሀገራቸውን አገልግለዋል።

ወ/ሮ ወይንሸት አበበ - (የትምህርት ዝግጅት በአርት የመጀመሪያ ዲግሪ)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ፀሐፊ ቀደም ሲል በደቡብ አዲስ አበባ እና በዋና መ/ቤት የገበያና ሽያጭ ክትትል ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የአስተዳደር ረዳት በመሆን አገልግለዋል፡፡ በሙያቸው የማርኬቲንግ ባለሙያ ሲሆኑ በተቋሙ ውስጥ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ አገልግለዋል።

ግብረ መልስ

አስተያየት
Scroll to Top