የተጫነው አቅም በምንጭ ተካፍሎ

ከውሃ 9213 MW
94.49%
ከንፋስ 504 MW
MWnntg 5.16%
ከእንፋሎት 7.3 MW
2500 KW 0.075%
ባዮማስ 25 MW
2500 KW 0.25%

ሃይል ማመንጨት

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ፈጣንና ተከታታይ ዕድገት ማስመዝገብ ችላለች፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ልማት ደግሞ ለዚህ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለማቋቋም በወጣውና በተሻሻለው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 381/2008 መሠረት ተቋሙ የኃይል ማመንጫዎችን፣ የኃይል ማስተላለፊያዎችንና የኃይል ማከፋፈያዎችን የመገንባት፣ የጅምላ ሽያጭ፣ የተስማሚነት ጥናት፣ የዲዛይንና የቅየሳ ሥራ የማከናወን ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ
አዳማ ንፋስ 1
ቆቃ
ጊቤ 3

በአሁኑ ጊዜ ተቋሙ 24 የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መካከል 16 ያህሉ ከውሃ ሲሆኑ እነሱም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (5130)፣ ጊቤ 3 (1870 ሜ.ዋ)፤በለስ (460 ሜ.ዋ)፤ ግልገል ጊቤ 2 (420 ሜ.ዋ)፣ ተከዜ (300 ሜ.ዋ)፣ ግልገል ጊቤ 1 (184 ሜ.ዋ)፣ መልካ ዋከና (153 ሜ.ዋ)፣ ፊንጫ (134 ሜ.ዋ)፣ አመርቲ ነሼ (95 ሜ.ዋ)፣ ጢስ ዓባይ 2 (73 ሜ.ዋ)፣ ቆቃ (43.2 ሜ.ዋ)፣ አዋሽ 2 (32 ሜ.ዋ)፣ አዋሽ 3 (32 ሜ.ዋ)፣ ጢስ ዓባይ 1 (11.4 ሜ.ዋ) አባ ሳሙኤል (6.6 ሜ.ዋ) እና ገናሌ ዳዋ 3 (254 ሜ.ዋ.) በድምሩ ከውሃ 4820.2 ሜጋ ዋት ያመነጫሉ፡፡

ከንፋስ ደግሞ አዳማ 2 (153 ሜ.ዋ)፣ አሸጎዳ (120 ሜ.ዋ) እና አዳማ 1 (51 ሜ.ዋ) እንዲሁም አሰላ (100 ሜ.ዋ) እና በከፊል ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ (80 ሜ.ዋ) በድምሩ 504 ሜጋ ዋት በማመንጨት ላይ ሲሆን ቀሪው ከእንፋሎትና ከዲዝል መጠባበቂያ የሚገኝ ነው፡፡

የማመንጨት አቅም በሜጋ ዋት (በ2015 ዓ.ም)

ተ.ቁየኃይል ማመንጫ ጣቢያውሃ (ሀይድሮ)ንፋስባዮማስጂኦተርማልጠቅላላስራ የጀመረበት ዓ.ም (እ.ኤ.አ)
21ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ515051502022
17ግልገል ጊቤ III187018702015
15በለስ4604602010
14ግልገል ጊቤ II4204202010
13ተከዜ3003002009
19ገናሌ ዳዋ2542542020
8ግልገል ጊቤ I1841842004
5መልካ ዋከና1531531988
4ፊንጫ134134.21973/2003
16አመረት ነሺ97952011
7ጥስ አባይ II73732001
1ቆቃ43.243.321960
2አዋሽ II3232.11966
3አዋሽ III32321971
6ጥስ አባይ I11.411.41964
23አዳማ II1531532014
22አሸጎዳ1201202012
28አሰላ1001002025
29አይሻ II802025
20አዳማ I51512012
24ረጲ የቆሻሻ ኃይል ማመንጫ25252019
9አሉቶ ላንጋኖ7.37.31999
10ቃሊቲ142004
11ድሬዳዋ402004
12አዋሽ 7 ኪሎ352004
25ድሬዳዋ (mu)3.61965
26አክሱም3.151975/1992
27አድዋ31998
ጠቅላላ (ICS Total)9213.6504257.39749.9
ድርሻ (%)94.495.160.250.07100

ግብረ መልስ

አስተያየት
Scroll to Top