የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር /EEP/DS/01/17
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አቅርቧል፤
ሎት-1- 08(ስምንት) ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፤ቦታ ኮተቤ አካባቢ ብረታ ብረት ፊት ለፊት ከሚገኘው የተቋሙ ዋና መ/ቤት ግቢ፤
ሎት-2- ለተቋማችን አገልግሎት የማይሰጡ የብረት፣ የተሽከርካሪና የማሽነሪ ስክራፖች፤(ሞተር እና ቻንሲ ቆራርጦ የሚረከብ) ፤ ቦታ ኮተቤ አከባቢ ብረታ ብረት ፊት ለፊት ከሚገኘው የተቋሙ ዋና መ/ቤት ግቢ እና አዳማ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግቢ፤
ሎት-3- የጠጠር ማምረቻ (መፍጫ) ክሬቸር ማሽን፤ቦታ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን መልካ ዋከና ኃ/ማመጫ ጣቢያ ግቢ፤
ሎት-4- ለመልካ ሰዲ የዕንፋሎት ኃ/ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት የመጡ ከፍተኛ መጠን፣ ዓይነትና ዋጋ ያላቸው ዕቃዎችና ማሽነሪዎች፤ ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መልካ ሰዲ ከተማ በፕሮጀክት ጣቢያ ቅጥር ግቢ፤
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፤
ማሳሰቢያ፡- ውድድሩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲየን ማህበር በፈጠሩት የማወዳደሪያ ሲስተም መተግበሪያ https://onelink.to/njnamp መሰረት መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲየን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት የተቋሙ ጣቢያዎች በመገኘት መመልከት ይቻላል፤
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች በሎት ሁለት ላይ ለመሳተፍ በብረት አቅላጭ ድርጅትነት የተሰማሩ መሆን ያለባቸው ሲሆን፤ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሰረት ሲሆን ፣ ለሎት ሁለት ብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን)፣ ለሎት ሶስት ብር 300,000.00(ሶስት መቶ ሺህ) እና ለሎት አራት ብር 500,000.00(አምስት መቶ ሺህ) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ከ27/03/2017 እስከ 11/04/2017 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡00 ድረስ ይካሄዳል ስለሆነም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታዉን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።
- ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
- በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ በሚገለፅላችሁ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት መፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፤
- ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ሊሰረዝ ይችላል፤
- ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-5511/ 011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 011-558-14-24 ወይም 011-558-06-49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ለበለጠ መረጃ አርብ ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ።ም የወጣዉን አዲስ ዘመን ጋዜጣ መመልከት ይቻላል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ – ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም