የጫካ ፕሮጀክት 132/15 ኪሎ ቮልት ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ እና ከጫካ – ኮተቤ – ቤላ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ከመሬት ስር ኃይል የማስተላለፊያ መስመር የመዘርጋት ፕሮጀክት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ለማስፋትና ለማዘመን ያላትን ቁርጠኝነት ለማሳየት የሚከናወን ግንባታ ነው።
የፕሮጀክቱ ዋና ክፍል ጫካን ከኮተቤ – ቤላ መስመር ጋር ለማገናኘት የሚከናወን የ5 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የመሬት ሥር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር መዘርጋት ነው፡፡ ይህ የመሬት ውስጥ የመስመር ዝርጋታ በአካባቢ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመቀነስ፣ ለዕይታ የሚያውኩ ነገሮችን ለማስወገድ እና የመልክዓ ምድርን አጠቃላይ ሥነ ውበት ለማሻሻል የሚያግዝ ነው።