የኢትዮጵያ-ኬንያ የሃይል ሲስተም ትስስር ፕሮጀክት; ከፍተኛ የቮልቴጅ ቀጥታ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት.

የፕሮጀክቱ ውጤት

ኢትዮጵያ በውሃ ኃይል ማመንጨት ያላትን ግዙፍ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የምስራቅ አፍሪካ እና ከዚያም አልፎ የቀጣናው የኢነርጂ ማዕከል ለመሆን መንግስት  እየሰራ ነው። የዚህ ተግባር አካል የሆነው የኢትዮ – ኬንያ የኃይል ትስስር ፕሮጀክት የምስራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሲሆን በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነና  ለአካባቢው የኃይል ትስስር ዋንኛ የጀርባ አጥንት ተደርጎ ይወሰዳል።

ፕሮጀክቱ የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚ በማሻሻል ዘርፈ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ሥራ ጀከመረ በኋላ ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘ ሲሆን በኬንያ አሁን ያለውን የኃይል እጥረት በማቃለል ላይ ይገኛል። ፕሮጀክቱ ከታንዛኒያ እና ከተቀረው የደቡባዊ አፍሪካ ጋር በኃይል ለመተሳሰር በር ከፍቷል።

Scroll to Top