ሪጅኑ የህፃናት ማቆያ ከፈተ

ሪጅኑ የህፃናት ማቆያ ከፈተ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ 1 ሪጅን የህፃናት ማቆያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ በድሩ አህመድ ማቆያ ማዕከሉ ለህፃናት ምቹ የሆነ ክፍል እና የተለያዩ ቁሳቁሶች የተሟሉለት መሆኑን ተናግረዋል።

የማቆያ ማዕከሉ የተቋሙ ሴት ሠራተኞችን የስራ ጫና ከመቀነስ ባሻገር የስራ ተነሳሽነታቸውንም እንደሚያሳድግ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በሪጅኑ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ተወካይ ወ/ሮ መሠረት ካሳ በበኩላቸው የማዕከሉ መከፈት ሴት ሠራተኞች ልጆቻቸውን በቅርበት እየተከታተሉ መደበኛ ሥራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ ይረዳል ብለዋል።

ለማዕከሉ እውን መሆን የተቋሙ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ፤ የሪጅኑ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን የተናገሩት ደግሞ የሪጅኑ የሰው ሀብት፣የንብረት አስተዳደር  እና ጠቅላላ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ተገኝ ናቸው።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top