የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በድርጅቱ በነበረው ክፍት የሥራ መደብ ላይ የውጭ ማስታወቂያ አውጥቶ ተወዳዳሪዎችን በጽሁፍ ፈተና መፈተኑ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሠረት መስፈርቱን አሟልተው ከተፈተኑት ተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ያመጡ እና ስማቸው በዝርዝር የተገለጸው ተወዳዳሪዎች ከመስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከቃሊቲ ብረታብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መሥሪያ ቤት የሰው ኃይል ቅጥርና ምደባ ቢሮ በመቅረብ የቅጥር ሂደታችሁን እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን።
የተወዳዳሪዎችን ሙሉ ዝርዝር ከታች ከተያያዘው ፋይል ላይ መመልከት ይችላሉ።