የERP ትግበራ ለተቋማዊ ራዕይ ስኬት ፕሮጀክት ዓባይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውስጥ አሰራሩን ለማዘመን ብሎም የአገልግሎት ጥራት ለመጨመር ERP የተሰኘ ሲስተም ለመተግበር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ይህ የሲስተም ትግበራ ስምምነት ፕሮጀክት ዓባይ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ወደ ስራ ገብቷል፡፡ ፕሮጀክት ዓባይን በተሳካ ሁኔታ ለመተግበር ከሁለቱም ተጨማሪ ያንብቡ…

በትግራይ ክልል በተካሔደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ከ240 ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ደርሷል

በትግራይ ክልል በተካሔደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ከ240 ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ ፡፡ የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮነን እንደገለፁት በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት በርካታ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡  የሰሜን ሪጅን በተከዜ እና አሸጎዳ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ውስጥ ተጨማሪ ያንብቡ…

ተቋሙ በጅማ ከተማ አዲስ ህንፃ ሊያስገነባ ነው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሰብስቴሽንና ትራንስሚሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ በጅማ ከተማ አዲስ ባለ 8 ፎቅ ህንፃ ሊያስገነባ መሆኑን ገለጸ፡፡ የቢሮው ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ገዛኽኝ እንደተናገሩት ህንፃው የሚገነባበት 2 ሺህ 500 ካሬ መሬት ቀደም ሲል የዲዝል ጄኔሬተር የሠራተኞች መኖሪያ የነበረ ነው፡፡ የግንባታው ቦታ የአፈር ጥናትና የዲዝይን ሥራዎች መጠናቀቁንና በቅርቡም ተጨማሪ ያንብቡ…

የሰኮሩ እና የጅማ 2 ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የኃይል ስርጭት በማሳለጥ ደረጃ ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ ናቸው

የሰኮሩ ባለ 400 ኪ.ቮ እና የጅማ 2 ባለ 230 ኪ.ቮ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን የኃይል ስርጭት በማሳለጥ በኩል ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ መሆናቸውን የጣቢያዎቹ ሥራ አስኪያጆች አስታውቀዋል፡፡ የሰኮሩ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ አንድነት ማሞ እንደተናገሩት የሰኮሩ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በሀገሪቱ ካሉ ግዙፍ ጣቢያዎች አንዱ መሆኑንና በአማካኝ ተጨማሪ ያንብቡ…

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 በመቶ ደረሰ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለፁ። ሚኒስትሩ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑትን ተግባራትና የህዳሴ ግድብን የግንባታ ሂደት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ዶክተር ስለሺ በመግለጫቸው እንዳመለከቱት የግድቡ ግንባታ የሲቪል ስራዎች አፈጻጸም 91 በመቶ ደርሷል። አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ አፈጻጸም ደግሞ 78 ተጨማሪ ያንብቡ…

ፕሮጀክቱ ሁለት አምቡላንሶችን በስጦታ እና በግዥ ማሟላቱን ገለፀ

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ለሚከሰት የኮቪድ 19 እና ሌሎች የጤና ሥጋቶች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያግዙ አንቡላንሶች መሟላታቸውን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ገለፁ፡፡ ለፕሮጀክቱ አንዱን አምቡላንስ በስጦታ ሌላኛውን አምቡላንስ ደግሞ በግዥ እንዲሟሉ ያደረገው የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር መሆኑን ኢንጂነር ክፍሌ ገልፀዋል፡፡ ይህም በግድቡ ግንባታ ወቅት ለሚያጋጥሙ የኮቪድ ተጨማሪ ያንብቡ…

ለግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኃይል ለማቅረብ እየተሰራ ነው

ለግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንደገለፁት ለምርቃት ዝግጁ ለሆነው ለቡሬ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ሁለት አማራጮች ተይዘው ጥናት ሲካሔድባቸው ቆይተዋል፡፡ ለፓርኩ ኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ከባህርዳር ማከፋፈያ ጣቢያ በዳንግላ- ተጨማሪ ያንብቡ…

በሳይት ላይ መስራት ያለበት ሥራ ተሰርቷል – የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ

የአይሻ II የንፋስ ኃይል ፕሮጀክት ከሚኖሩት 48 የንፋስ ተርባይኖች መካከል የአርባዎቹን ተርባይኖች ተከላና የፍተሻ ሥራ በተያዘው በጀት ዓመት በማጠናቀቅ ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ለማገናኝት እየሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ሙሉቀን ተሰማ እንደገለፁት በፕሮጀክቱ 120 ሜጋ ዋት ለማመንጨት ከሚተከሉት 48 የንፋስ ተርባይኖች መካከል የ24ቱ ተከላ ሙሉ ተጨማሪ ያንብቡ…

ከተቋሙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ውስጥ 33 ነጥብ 1 በመቶዎቹ በራስ አቅም የተገነቡ ናቸው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችንና የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን በራስ ኃይል የመገንባት አቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን የሲቪል ስራዎች ቢሮ ገለፀ፡፡ የቢሮው ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ኃይለ ጊዮርጊስ እንደገለፁት ተቋሙ ከባለ 45 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን በራስ ኃይል መገንባት የጀመረው ከ1973 ዓ.ም ጀምሮ ነበር፡፡ ቢሮው በሰው ተጨማሪ ያንብቡ…

ሪጅኑ ባለፉት 6 ወራት ከዕቅዱ በላይ የቅድመ ብልሽት ፍተሻና የጥገና ሥራ አከናወነ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምስራቅ ሪጅን የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ ባለፉት 6 ወራት የዕቅዱን 102 ነጥብ 38 በመቶ የቅድመ ብልሽት ፍተሻና የጥገና ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ፡፡ ቢሮው የስድስት ወር አፈፃፀሙን በጅግጅጋ ሲገመግም ዳይሬክተሩ አቶ ጋሻው እንድሪያስ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን ከዛፍ ንኪኪ የማፅዳት፣ የተሰበሩ ኢንሱሌተሮችን በሌላ ተጨማሪ ያንብቡ…

Facebook