የቱሉሞዬ ጂኦተርማል ፕሮጀክት የመጀመሪያው ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቋል

በአርሲ ዞን ኢተያ አካባቢ የተጀመረው የቱሉሞዬ የከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይል ማመንጫ ግንባታ ፕሮጀክት 150 ሜጋዋት ኃይል ለማግኘት በሁለት ምዕራፎች እየተከናወነ ነው፡፡ የቱሉሞዬ ጂኦተርማል ኢነርጂ የቴክኒክ ኃላፊ ስጉርጉር ጌሪሰን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ የምትገኝ ሀገር በመሆኗ  የእንፋሎት ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ከፍተኛ እምቅ አቅም አላት፡፡ በቱሉሞዬም እስከ 2000 ሜጋ ዋት ተጨማሪ ያንብቡ…

የአሉቶ ጂኦተርማል የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሚያዝያ 10 የጉድጓድ ቁፋሮው ይጀመራል

የአሉቶ ላንጋኖ ጂኦተርማል የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሚያዝያ 10 ቀን 2013 ዓ/ም የጉድጓድ ቁፋሮ እንዲጀመር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ አቅጣጫ አስቀመጡ። ለሥራው መጀመር የውሃ አቅርቦት ወሳኝ በመሆኑ ቀሪ ስራዎቹ  በፍጥነት እንዲጠናቀቅም ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ንጉሴና ፕሮጀክቱን በፋይናንስ የሚደግፈው የዓለም ባንክ ተወካዮች ተጨማሪ ያንብቡ…

ተቋሙ ለጥገና ስራ ያወጣ የነበረውን ወጪ የሚታደግ ሥራ እየተሰራ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለውሃ ፓምፕ ጥገና ያወጣ የነበረውን ተጨማሪ ወጪ መቀነስ መቻሉን የጢስ አባይ 1 እና 2 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አስታወቀ፡፡         የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ጉታ እንዳስታወቁት ኃይል ማመንጫዎች ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የውሃ ፓምፖችን ለማስጠገን በጨረታ ለአንድ ፓምፕ 95 ሺህ ብር ዋጋ ቀርቦ ነበር፡፡     ይሁን እንጂ የጢስ አባይ 2 ተጨማሪ ያንብቡ…

የጊንጪ ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተመረቀ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የጊንጪ ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን በዛሬው ዕለት በይፋ  መርቀዋል። በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ላይ አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንደተናገሩት የማከፋፈያ ጣቢያው በአካባቢው የሚስተዋለውን የኃይል አቅርቦት ችግር ለመፍታትና  በአካባቢው ኢንቨስትመንት እንዲስፋፉ ለማድረግ ያግዛል። መንግስት በመላው ኢትዮጵያ የልማት ችግሮችን ለመፍታትና የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል ተጨማሪ ያንብቡ…

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የኢትዮጵያውያን ህልውና መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

የታላቁ ኢትዮጵያ  ህዳሴ ግድብ ግንባታ የኢትዮጵያውያን ህልውና መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።     የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ በስካይላይት ሆቴል በተዘጋጀ ሀገር አቀፍ ሲምፓዚየም  ላይ  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት  የዓባይ ተፋሰስ የሃገሪቱን ሁለት ሶስተኛውን የውሃ ተፋሰስ የሚሸፍን በመሆኑ ዓባይን የማልማት ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ነው። ግድቡ መላው ኢትዮጵያውያን ተጨማሪ ያንብቡ…

ዋና ሥራ አስፈፃሚውና አምባሳደሩ የመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ጎበኙ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ጎበኙ፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ አሸብር ባልቻ ጣቢያው ከ30 ዓመት በላይ ያገለገለ በመሆኑ የማሻሻያ ሥራዎች እንደሚፈልግ ለአምባሳደሩ ገልፀውላቸዋል፡፡ የጣቢያውን አቅም ለማሳደግ ቀደም ሲል የመግባቢያ ሥምምነት መፈረሙን በማስታወስ የተጀመሩት ቴክኒካል ጥናቶች ሂደቶች እንዲፋጠኑና ለማሻሻያ ስራው ተጨማሪ ያንብቡ…

ሴቶች ለመልካም ማህበረሰብ ግንባታ ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ ነው ተባለ

ሴቶች በተቋማዊ እና ሀገራዊ ግንባታ ካላቸው ግንባር ቀደም ሚና ባለፈ ለመልካም ማህበረሰብ ግንባታ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የንብረትና አገልግሎት ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ስመኝ አያሌው ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት አድርገው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ሴቶች በልጆች አስተዳደግ እና በቤተሰብ አስተዳደር ያላቸው ችሎታ እና አስተዋይነት ለመልካም ማህበረሰብ ግንባታ ተጨማሪ ያንብቡ…

የኤሌክትሪክ ኃይልን ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ ማድረግ ይገባል – የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር

የጃዊ – በለስ ባለ 132/33 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ  መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ትናንት ተመርቋል፡፡   በምርቃት ሥነ – ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አቅሙን በየጊዜው እያሳደገ የሀገሪቱን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት እየሰራ ያለው ሰራ የሚበረታታ ነው፡፡   ይሁን እንጅ በክልሉ ተጨማሪ ያንብቡ…

የማከፋፈያ ጣቢያው ግንባታ 68 በመቶ ደርሷል

በማሻ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የማሻ – መቱ ባለ 230/33 ኪ.ቮ. የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈጻጸም 68 በመቶ መድረሱን የማከፋፈያ ጣቢያው የሳይት ተቆጣጣሪ መሐንዲስ አቶ ፍቃዱ ሁጤሳ ገለፁ፡፡ መሐንዲሱ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ አንድ አዲስ ባለ 230/33 ኪ. ቮ. ከፍተኛ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና 161 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው የባለ ተጨማሪ ያንብቡ…

Facebook